top of page
Picture4.png

እንኳን ደህና መጣችሁ!

Hi ሳሚ ነኝ...

Hi ሳሚ ነኝ! ሞቲቬሽናል ስፒከር እና ስኬታማ ቢዝነስ ባለቤት ነኝ፣ ከሁሉ በላይ አባት ነኝ። ይሄንን የምስጋና ማስታወሻ ለማዘጋጀት ስነሳ፣ በህይወቴ ትልቅ ለውጥ እንዲፈጠር ከረዱኝ እና ከጠቀሙኝ፣ ከራሴ የሕይወት ተሞክሮ እንዲሁም በትምህርት ካገኘሁዋልቸው እና ካነበብኩዋቸው መፃፍት እና፣ ካካበትኩዋቸው ልምዶች ተነስቼ ለእናንተ ለወገኖቼ ይጠቅማል በማለት ይሄንን የምስጋና ማስታወሻ ሳቀርብ በደስታ ነው።


ይህ የመጀመርያውና ብቸኛው በአማርኛ የተፃፈ የምስጋና ማስታወሻ ነው። 

ይህ ማስታወሻ በቀን የ10-ደቂቃ የጥሞና ጊዜ በመውሰድ በምስጋና፣ በአላማ እና በማስተዋል እንድትኖሩ የሚረዳ ነው!

Cover
Inside
Inside
Goal
Goals
Strength

የምስጋና ጥቅም

ምስጋና ደስታን ይጨምራል! ያሉንን ነገሮች አውቀን ስናመሰግን፣ ደስተኛ ከመሆን ባሻገር ፣ ያሉን ነገሮች በቂ ይሆናሉ። ስለዚህ ይህን ማስታወሻ በመጠቀም፣ ማለዳ 3-የምታመሰግኑባቸውን ምክንያቶች በመፃፍ፣ ምስጋና የተሞላበትን ሕይወት መኖር ጀምሩ። ለምሳሌ :-  “ዉሃ ቀድቼ መጠጣት ችያለሁ አመሰግናለሁ” በሉ።

መልካም ቃላትን የመናገር ጥቅም

አዎንታዊ የሆኑ ቃላትን ለራስ መናገር ትልቅ ኃይል አለው። ቃል ደግሞ ዘር ነው። ስለዚህ ስለራሳችን በተደጋጋሚ የምንናገራቸው መልካም ቃላቶች ሕይወታችን፣ ባሕርያችን ፣ ስሜታችን ፣ እና ድርጊታችን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያመጣ አውቃችሁ፣ ይህንን ማስታወሻ በመጠቀም እለት እለት ለራሳችሁ መልካም ነገርን መፃፍ፣ መናገር ጀምሩ።

ለራስ እንክብካቤን የማድረግ ጥቅም

ጥድፊያ በበዛበት ዓለም፣ በትምህርት፣ በስራ፣ ልጅ በማሳደግ፣ በኑሮ፣ ቤተሰብ በመርዳት እና በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ ተጠምዳችሁ፣ እራሴን ረስቼው ቢሆንስ ብላችሁ ታውቃላችሁ? እናንተ ደስተኛ፣ ጤነኛ እና ስኬታማ ስትሆኑ፣ አካባቢያችሁ ላሉ ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ ሁሉ ደስተኛ፣ ጤነኛና፣ ስኬታማ እንዲሆኑ መንገድ ትሆናላችሁ። እለት እለት፣ አንድ መልካም ነገርን በማድረግ፣ ራሳችሁን መንከባከብ ጀምሩ።

እለት እቅድ ማውጣት ጥቅም

አላማ ያለው ሰው ጠዋት ሲነቃ የሚያደርጋቸው ነገሮች ይታወቃሉ። ስለዚህ ይህን ማስታወሻ በመጠቀም፣ በዛን ቀን ልታሳኩዋቸው የሚገባችሁን 3-ነገሮችን በመፃፍ ማሳካት ስትጀምሩ፣ ከተወሰኑ ሳምንታት እና ወራት በሁዋላ ሕይወታችሁ፣ አሁን ካለበት የተሻለ እና ስኬታማ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም።

inside1.png

Contact Us

ጥያቄ ካሎት ያግኙን

Thanks for submitting!

Books and Coffee
bottom of page